ሚኒስትሯ የከተሞች እድገት ከመሪዎች፣ ባለሃብቶችና ነዋሪዎች የሚቀዳ ነው አሉ

,

የከተሞች እድገት ከከተማ መሪዎች፣ ባለሃብቶች ብሎም የከተሞች ነፀብራቅ ከሆነው ነዋሪ የሚቀዳ ነው ሲሉ የከተማና መሰረተ-ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ ተናግረዋል፡፡

“ተግዳሮቶችን የሚቋቋሙ ከተሞች በኢንተርፕሪነርሺፕ በተቃኘ ተግባር ለከተሞች ተግባር ለከተሞች መነቃቃትና ዕድገት የከንቲባዎች ሚና” በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ ነው፡፡

ከንቲባዎች፣ የንግድ ምክር ቤት አመራሮች እንዲሁም የንግድ አንቀሳቃሾች ያሉበትን እንቅስቃሴ በመገምገም ለንግድ መስፋፋት የሚረዱ ፈጠራ የታከለባቸው ፖሊሲዎችን፣ ለምጣኔ ሃብቱ አስተዋጽኦ ያላቸው መመሪያዎችንና ደንቦችን ማውጣትና መተግበር ለከተሞች እድገት ከፍተኛ ሚና እንዳለውም ሚኒስትሯ አክለው ገልፀዋል፡፡

የግሉ ዘርፍ በከተሞች እድገትና ነዋሪዎች ህይወት መለወጥ ውስጥ የሚኖረው ሚና የጎላ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

በመድረኩ 12ኛው የኢትዮ-ቻምበር ዓለም ዐቀፍ ኤግዚቢሽን በነገው እለት “ኢትዮጵያን ይግዙ በኢትዮጵያ ኢንቨስት ያድርጉ” በሚል መሪ ሃሳብ እንደሚጀመርም ተጠቁሟል፡፡

በውይይቱ ላይ የንግድና ቀጠናዊ ጉዳዮች ሚኒስትር ገ/መስቀል ጫላን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡

ግንቦት 24/2014 (ዋልታ)

በአመለወርቅ መኳንንት